የማይክል ሀኪም ክስና ቤተሰቦቹ3 የካቲት 2002ረቡዕ፣ የካቲት 3 2002ታዋቂው የፖፕ ሙዚቃ ንጉስ ማይክል ጃክሰን ሆን ተብሎ ተገድሏል ብለው እንደሚያምኑ ወላጅ አባቱ አስታወቁ ። በርሳቸው ዕምነት ሁሉ ነገር በሀኪሙ ላይ ተላከከ እንጂ ለማይክል ሞት ተጠያቂ የሆኑ ሰዎች ከጀርባ አሉ ።https://p.dw.com/p/LyFTማይክል ጃክሰንምስል APማስታወቂያበዶክተሩ ላይ ክስ የመሰረተው አቃቤ ህግ ግን ይህን መላምት የሚያረጋግጥ ማስረጃ የለውም ። ባለፈው ዓመት ሰኔ 18 ቀን 2001 ዓ ም ከዚህ ዓለም በሞት በተለየው በማይክል ጃክሰን የግል ሀኪም ላይ የተመሰረተው ክስ እንዳላረካቸው ሌሎች የቤተሰቡ አባላትም ተናግረዋል ። አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ። አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ ሸዋዬ ለገሠ