ሌላ የመብራት ተስፋ
ዓርብ፣ ግንቦት 23 2011ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ የሕዝብዋን የኃይል ፍጆታ የሚያረካ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ እንደሚገነባላት ቃል ሲገባ፣ ተስፋ ሲሰጥ፣ ቃል ተስፋዉ ሲበን ዓመታት ተቆጠሩ።የኢትዮጵያ ሕዝብ በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ዘንድሮም መብራቱ የኩራዝ ነዉ።ከኩራዝ ተላቅቋል ወይም የኤሌክትሪክ ኃይል ያገኛል የሚባለዉ የየከተማዉ ሕዝብም መብራት የሚያገኘዉ በቁነና ነዉ።ዛሬም ግን የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት «ኩራዛሕ በኤሌክትሪክ ኃይል ሊለወጥ ነዉ ይሉታል-ሕዝቡን።ባለስልጣናት እንደሚሉት ለ12 የገጠር ከተሞች መብራት የሚሰጡ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ግንባታ በቅርቡ ይጀመራል።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ