1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ጊዚያዊ ሁኔታ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 17 2006

የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ውዝግብ እየተባባሰ ሄዶ በሀገሪቱ ምስቅልቅሉ ሁኔታ እና ሥርዓተ አልባነት ተስፋፍቶዋል። ሕዝቡ፣ በተለይ ሴቶች እና ሕፃናት ለቀድሞ የሴሌካ እና ለሌሎች ዓማፅያን ቡድኖች ጥቃት ተጋልጦዋል።

https://p.dw.com/p/1AP3a
Young people patrol with rifles near a house destroyed by fire on October 11, 2013 in Bogangolo (171 km from Bangui). The Central African Republic, one of the poorest countries on the planet with a long history of instability, has descended into anarchy since rebels overthrew president Francoise Bozize in March 2013. Violence has surged between ex-rebels of the Seleka coalition that led the coup -- who are Muslim -- and local vigilante groups formed by Christian residents in rural areas. AFP PHOTO / PACOME PABANDJI (Photo credit should read PACOME PABANDJI/AFP/Getty Images)
ምስል PACOME PABANDJI/AFP/Getty Images

ሀገሪቱ ወደ ጅምላ ጭፍጨፋ የምታመራበት ስጋት መደቀኑንም ነው ዓለም አቀፉ ማህበረ ሰብ እያስጠነቀቀ ያለው። ይህንንም ተከትሎ አንድ ከፍተኛ የተመድ ባለሥልጣን በማዕከላይ አፍሪቃ የሚገኘው የአፍሪቃ ህብረት ጓድ ሊጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።

የሴሌካ ዓማፅያን ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር የቀድሞ የሀገሪቱን ፕሬዚደንት ፍራንስዋ ቦዚዜን በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ካስወገዱ በኋላ በሀገሪቱ በሚሼል ጆቶጂያ የሚመራ የሽግግር መንግሥት ተቋቁሞዋል። የታጠቁ፣ በብዛት ሙሥሊሞች የሆኑ የቀድሞዎቹ ያማፅያን ቡድኖች ብዙውን የሀገሪቱን ከፊል ተቆጣጥረዋል። እርግጥ፣ ከሽግግሩ መንግሥት ምሥረታ በኋላ የሀገሪቱ መሪ ሚሼል ጆቶጂያ ያማፀያኑን ቡድንኖች በመበተን በብሔራዊው ጦር ውስጥ ቢያዋህዱም፣ ከሴሌካ ዓማፅያን ጋ ግንኙነት የነበራቸው ቡድኖች አሁንም በርካታ መንደሮችን እያጠቁ ሲቭሉን ሕዝብ በማሸበር ላይ እንደሚገኙ ተገልጾዋል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ፣ ሂውማን ራይትስ ዎች ባልደረባ የቡድኑን ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን አስጠንቅቋል።
« ሂውማን ራይትስ ዎች የቀድሞ የሴሌካ ዓማፅያን በርካታ አስከፊ ወንጀሎችን መፈፀማቸውን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ሰብስቦዋል። በብዙ የሀገሪቱ አካባቢዎች፣ መዲናዋን ባነግዊን ጨምሮ የሚገኙት እነዚሁ ዓማፅያን ባሁኑ ጊዜ ከቁጥጥር ውጭ ሆነዋል። በመጨረሻ የመዘገብነው አሰከፊ ወንጀል በጋጋ አካባቢ፣ ኦምቤላምቦኮ በተባለ መንደር ሲሆን በዚያ የሴሌካ ዓማፅያን በመንደሩ ላይ ጥቃትበመሰነዘር በነዋሪዎቹ ላይ እጅግ አስከፊ ወንጀል ፈፅመዋል። »
በባንግዊ የሚገኘው የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ሽግግር መንግሥት በሀገሩ እየተባባሰ የመጣው ውዝግብ እንዲያበቃ እና ለሲቭሉ ሕዝብ ጥበቃ እስካሁን ያደረገው ጥረት በቂ ሆኖ አልተገኘም፣ እንዲያውም አቅም አልባ መሆኑን ነው የገለጹት።
« አዲሶቹ የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ባለሥልጣናት አንድም በአቅም መጓደል ይሁን በፍላጎት እጦት የተነሳ ሁኔታውን በሚገባ መቆጣጠር አልቻሉም። እነዚህ ሕዝቡን የሚያሸብሩትን የተለያዩ ቡድኖችን ማን እንደሚቆጣጠር በርግጥ አይታወቅም። እና እኛ እያልን ያለነው በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ አሁን ዓማፀያኑ እየፈፀሙት ያለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ ለፕሬዚደንት ጆቶጂያ ይህንኑ አስከፊ በደል ለማስቆም ቆርጠው መነሳታቸውን ለማሳየት የሚፈተኑበት ጥሩ አጋጣሚ ነው። »
እንደ ሂውመን ራይትስ ዎች፣ መንግሥት ተጠያቂዎቹን ይዞ ለፍርድ እንዲያቀርብ ጠይቀዋል።
ይኸው ሁኔታ ያሳሰባቸው የተመድ ምክትል ዋና ፀሐፊ ጃን ኤሊያሰን ባማፅያኑ ጥቃት በተለይ ሴቶች እና ሕፃናት መጎዳታቸውን በማስታወቅ ዓለም አቀፉ ማህበረ ሰብ አንድ ርምጃ ካልወሰደ ሁኔታው የከፋ ሊሆን፣ ብሎም ወደ ሀይማኖት እና ጎሳ ግጭት ሊቀየር እና ወደሌሎች አካባቢዎችም ሊስፋፋ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ኤልያሰን በመቀጠልም የተመድ ፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ያለውን የአፍሪቃ ህብረት ጓድ እንዲያጠናክር ጠይቀዋል። የቀድሞ የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ቅኝ ገዢ ፈረንሳይም ለጓዱ ማጠናከሪያ 1000 ወታደሮች ላጭር ጊዜ እንደምትልክ የመከላከያ ሚንስትር ዣን ኢቭ ለ ድሪዮን ገልጸዋል። ፈረንሳይ በወቅቱ 400 ወታደሮች በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ አሰማርታለች።

A French soldier inspects a car at a checkpoint at the Mpoko airport in Bangui November 23, 2013. World powers, led by France, are scrambling to contain a crisis that Paris and U.N. officials have warned could lead to genocide in Central African Republic, which slipped into chaos after rebels ousted the president in March. REUTERS/Joe Penney (CENTRAL AFRICAN REPUBLIC - Tags: POLITICS MILITARY) Bangui ist die Hauptstadt der Zentralafrikanischen Republik. Mit 542.393 Einwohnern (Berechnung 2005) ist Bangui die größte Stadt sowie das politische, wirtschaftliche und kulturelle Zentrum des Landes.
ምስል Reuters
Residents, who had found refuge in a nearby forest during clashes, go about their daily chores on October 8, 2013 after returning to Bangassou. The Central Africa Republic has been shaken by a recent increase in clashes between ex-rebels of the Seleka coalition that led the coup, who are Muslim, and local self-defense groups formed by rural residents who are Christian, in common with around 80 percent of the population. The poor but mineral-rich nation was plunged into chaos when a coalition of rebels and armed movements ousted longtime president Bozize and took the capital Bangui in March. AFP PHOTO / ISSOUF SANOGO (Photo credit should read ISSOUF SANOGO/AFP/Getty Images)
ምስል Issouf Sanogo/AFP/Getty Images

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ