የማኅበራዊ መገናኛ አጠቃቀምና የጠ/ሚ መግለጫ
ረቡዕ፣ መጋቢት 11 2011ማስታወቂያ
DW ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች መግለጫውን እርስ በእርሱ የተምታታ እና ግራ መጋባትን የያዘ እንዲሁም ማስፈራሪያ የታከለበት ነው ብለውታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው የማኅበራዊ መገናኛዎች አጠቃቀም ኢትዮጵያን አደጋ ላይ የሚጥል አዝማሚያ ጎልቶ መታየቱን ጠቅሰው ዘርፉ ሀገሪቱን ለመገንባት እና ለማዳን ሊውል ይገባል ብለዋል። ከአዲስ አበባ ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ሰሎሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሰ
አዜብ ታደሰ