የማስተማሪያ መፅሐፍት እጥረት በኢትዮጵያ
ማክሰኞ፣ መስከረም 23 2004ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምሕር ቤቶች ተማሪና መምሕራን በማስተማሪያ መፅሐፍት እጥረት መቸገራቸዉን አስታወቁ።የማስተማሪያ መፅሐፍት አለመኖር ተማሪዎችን ከየትምሕርት ቤቱ ሲያስቀር መምሕራን ደግሞ በእቅድ እንዳንመራ አስገድዶናል ይላሉ።አንዳድ ወላጆች መደበኛ ሥራቸዉን እያቋረጡ መፅሐፍት ፍለጋ በየመደበሩ መንከራተት ግድ ብሏቸዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት ለዘንድሮዉ የትምሕርት ዘመን በቂ የመማሪያ መፅሐፍት ማሰተሙን በሚቆጣጠራቸዉ መገናኛ ዘዴዎች እያስታወቀ ነዉ።የአዲስ አባባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ እንደዘገበዉ ግን የማስተማሪያ መፅሐፍት በጥቁር ገበያ እስከ መቶ ብር ይቸበቸባሉ።
ታደስ እንግዳዉ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ