የሙስሊሞች ተቃዉሞና የፖሊሶች ግድያ13 ጥቅምት 2005ማክሰኞ፣ ጥቅምት 13 2005ደቡብ ወሎ ገርባ ከተማ በሚኖሩ ሙስሊሞችና በፖሊስ መካካል ባለፈዉ ዕሁድ በተደረገ ግጭት በትንሹ አራት ሰዎች ተገደሉ።የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ለፈረንሳዩ ዜና አገልግሎት እንደነገሩትhttps://p.dw.com/p/16VJmምስል picture alliance/dpaማስታወቂያ ግጭቱ የተነሳዉ ተቃዋሚዎች ፖሊስ ጣቢያን ከበዉ ፖሊሶች ላይ ጥይት በመተኮሳቸዉና ፖሊሶችን በቆንጨራ ለመደብደብ በመሞከራቸዉ ነዉ።በግጭቱ ከተገደሉት አንዱ ፖሊስ መሆኑን አቶ ሽመልስ አስታዉቀዋል።በስልክ ያነጋግርናቸዉ የአይን ምስክሮች እንደሚሉት ግን ግጭቱ የተፈጠረዉ ገርባ መስጊድና አካባቢዉ ነዉ።ሁለቱን አነጋግረናል። ገመቹ በቀለ ነጋሽ መሀመድ ሸዋዬ ለገሰ