የመዋዕለ ህፃናት እጥረት በጀርመን
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 3 2003ማስታወቂያ
ይሁንና አሁንም ጀርመን ውስጥ የሚወለዱ ህፃናት ቁጥር ከመጨመር ይልቅ እየቀነሰ መሆኑን የፌደራል ጀርመን ስታስቲክስ ፅህፈት ቤት ባለፈው ሳምንት ያወጣው አንድ ዘገባ ያመለክታል ። በዚሁ ዘገባ መሠረት ባለፈው የጎሮጎሮሳውያኑ 2010 ዓ.ም እድሜያቸው ከ 18 ዓመት በታች የሆነ ህፃናት ቁጥር ከዛሬ 10 ዓመቱ አሃዝ ጋር ሲነፃፀር በ 14 በመቶ ያነሰ ነው ። ለዚህም የልጆች መዋያ ቦታዎች እጥረት አንድ ምክንያት ሆኖ ይቀርባል ። የዶቼቬለዋ Daphne Grathwohl እንደዘገበችው በአሁኑ ሰዓት ጀርመን ውስጥ ከ 3 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት መዋያ ፈልጎ ማግኝት የስራ ፍለጋ ያህል ከብዷል ።
ሂሩት መለሰ
ሸዋዮ ለገሰ