የመኢአድ አቤቱታና የምርጫ ቦርድ መልስ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 6 2006ማስታወቂያ
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ በደቡብ ክልል አባላቱ እስር ወከባና ልዩ ልዩ የመብት ጥሰቶች ይፈፀሙባቸዋል ሲል አማረረ ። የድርጅቱ አመራር አባላት ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በአሁኑ ጊዜ በደቡብ ክልል 16 የአመራር አባላት በእሥር ላይ ይገኛሉ ። በክልሉ የመኢአድ አባላት ከእስር ሌላ በአንዳንድ አካባቢዎች ስብሰባ ማድረግ እንደሚከለከሉና በአጠቃላይ የመደራጀት መብታቸው እንደተነፈገ አመራሮቹ አስታውቋል ። የክልሉ የምርጫ ቦርድ በበኩሉ የሚደርሱትን አቤቱታዎች አጣርቶና ተከታትሎ ለፌደራል ምርጫ ቦርድ እንደሚያሳውቅ በፍትህ አካላት በተያዙት ጉዳዮች ግን ጣልቃ እንደማይገባ መልስ ሰጥቷል ። ሆኖም ሰሞኑን የቀረበ ቅሬታ መኖሩን እንደማያውቁ የገለጹት የደቡብ ክልል ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ከዚያ ቀደም ሲል ግን በፖለቲካ ምክንያት የታሰረ ሰው እንደሌለ ተናግረዋል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ