የመኖርያ ቤት እጦትና የቤት ኪራይ ዋጋ ንረት
እሑድ፣ ጥር 15 2008ማስታወቂያ
አንዳንድ ቤት አከራዮች ደግሞ አጋጣሚዉን በመጠቀም የቤት ኪራይ ዋጋ በየጊዜዉ እየጨመሩ ተከራዮችን ያማርራሉ። የከተሞች መጨናነቅ የሕዝብ ብዛት የከተማ መስተዳድሮች ለየከተማዉ መስፋፋት የሚያከናዉኑዋቸዉ ተግባራት ከሕዝብ ቁጥር እድገት ወይም ከሕዝብ ፍላጎት ካለመጣጣሙ ጋር በከተሞች አካባቢዎች የተለያዩ የመሠረተ ልማት አካባቢዎች የተለያዩ የመሠረተ ልማት ችግሮች ጎልተዉ ይታያሉ። የመጠጥ ዉኃ ፤ የትራንስፖርት የመፀዳጃና የመሳሰሉት ችግሮች በተደጋጋሚ የሚነሱ ናቸዉ። ከነዚህ ሁሉ የከፋዉ ግን የመኖርያ ቤት ችግር ነዉ። አንዳንድ ቤት አከራዮች ደግሞ አጋጣሚዉን በመጠቀም የቤት ኪራይ ዋጋ በየጊዜዉ እየጨመሩ ተከራዮችን ያማርራሉ። የችግሩ ምክንያት ምንድን ነዉ፤ መፍትሄዉስ? በጉዳዩ ላይ አቶ መስፍን መንግሥቱ የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ ወ/ሮ አያልሰዉ ወርቅነህ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ተወካይ፤ አቶ ኤፍሪም ቦተሪ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሣይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ እንዲሁም ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩን ጋብዘናል።
የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ሙሉዉን ዉይይት እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ