የመንግሥታቱ ድርጅት የኤርትራና የሶማሊያ ተቆጣጣሪ ዘገባ
ዓርብ፣ ሐምሌ 13 2004ማስታወቂያ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራና የሶማሊያ ተቆጣጣሪ ቡድን ኤርትራ ለሶማሊያው አማፂ አሸባብ ቀጥተኛ ድጋፍ ስለማድረጓ ማስረጃ እንዳላገኘ ገለፀ ሆኖም ቡድኑ ኤርትራ በድብቅና በእጅ አዙር የመሣሪያ ዝውውር የወታደራዊ ሥልጠና ና የገንዘብ እርዳታ ማድረጓን ሳትቀጥል እንዳልቀረች አስታውቋል ። ቡድኑ ነፃ ና ገለልተኛ አይደለም የምትለው ኤርትራ ክሱን መሰረተ ቢስ ስትል አጣጥላዋለች ። በተባበሩት መንግሥት ድርጅት የኤርትራ አምባሳደር አቶ አርአያ ደስታ ቡድን የወጣው ዘገባ ኤርትራን ለማጥቃት ያሰበ ይመስላል ብለዋል ዝርዝሩን አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ልኮልናል ።
አበበ ፈለቀ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ