የመንን ሥጋት ላይ የጣለዉ የኮሌራ ወረሽኝ
ዓርብ፣ ሐምሌ 14 2009ማስታወቂያ
ሥርጭቱን ለመግታት አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደም በሽታዉ ባጭር ጊዜ ዉስጥ ከሩብ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ሊለክፍ እንደሚችል ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። ሳዑዲ አረቢያ መራሹ የአረብ ሃገራት ጦር የመንን መደብደብ ከጀመረ ከካቻምና መጋቢት ወር ጀምሮ የተባባሰዉ ጦርነት ከ8 ሺህ በላይ ሕዝብን ፈጅቷል፤ ከ 45 ሺህ ሕዝብ በላይ ደግሞ አቁስሏል። ሰንዓ የሚገኘዉ ተባባሪ ዘጋቢ ግሩም ተክለሃይማኖት እንደገለፀልን ደግሞ ከኮሌራ ወረርሽኝ በሽታ በተጨማሪ ሰሞኑን በሀገሪቱ የዓይን ሕመም እየተሰራጨ ነዉ። አዜብ ታደሰ ስለጉዳዩ ግሩምን ቀደም ብላ በስልክ አነጋግራዉ ነበር።
ግሩም ተክለ ሃይማኖት
አዜብ ታደሰ