የመቅደላ ጥንታዊ ቅርሶች ያስነሳዉ ዉዝግብ
የብሪታንያ ጦር እንደ ጎርጎሪያኑ1868 ኢትዮጵያ በወረረበት ወቅት ከኢትዮጵያ የዘረፋቸዉ በርካታ ጥንታዊ ቅርሶች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተዘንግተዉ ነበር። አሁን ግን ትኩረት በመሳባቸዉ ዉዝግብ አስከትለዋል። እነዚህን የሚቆጣጠሩት ተቋማት ቅርሶችን እንደያዙ በማቆየትና ለጎብኚዎች ማሳያታቸዉን በቀጠሉ ኃላፊነት አጣብቂኝ ዉስጥ ገብተዋል።
ንጉሣዊ ብልፅግና
ለንደን የሚገኘዉ ዝነኛዉ በቪክቶርያ እና አልበርት ቤተ-መዘክር ባለፈዉ ሚያዝያ 27 ከኢትዮጵያ የተዘረፉትን ቅርሶች ለሕዝብ የሚያሳይ ዓዉደ ርዕይ መከፈቱ፤ ቅርሶቹ የት መቀመጥ አለባቸዉ የሚል አዲስ ክርክር አስነስቷል። ቅርሶቹ የብሪታንያ ጦር እና የአፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት እንደ ጎሮጎርያኑ አቆጣጠር በ1968 ባደረጉት ዉጊያ ወቅት የብሪታንያ ጦር ከዘረፋቸዉ መካከል 20 ንጉሣዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶች ይገኙበታል።
የቀድሞዉ የብሪታንያ ጦር ሠራዊትና ያስነሳዉ ዉዝግብ
የብሪታንያ ወታደሮች በመቅደላ።የብሪታንያ ጦር ድል ካደረገ በኋላ የፈለገዉን መዝረፍ ችሎ ነበር። ልቅ ዘረፋዉ በወቅቱ ኢንግላድ ዉስጥ ሳይቀር ዉዝግብ እና ሐፍረት አስከትሎ ነበር።«የእነዚህ ጥንታዊ ቅርሶች የተገኙበትን ትክክለኛ ሥፍራ በማንፀባረቅ፤ እና ታሪካቸዉን በማሳወቅ አስቸጋሪ እና ዉስብስቡን ሐቅ መጋፈጥ እንደልጋለን።»ሲሉ የቪክቶርያና አልበርት ቤተ-መዘክር ዳይሬክተር ትሪስትራም ሁንት ተናግረዋል።
ያለፈዉን መጋፈጥ
የተዘረፉ ቅርሶችን ወደየመጡበት ሥፍራ የመመለሱ ዉስብስብ እሳቤ እና ምግባር በአውሮጳና በዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ለበርካታ ዓመታት ሲያነጋግር ነበር። ለዉጤት ግን አልበቃም። አሁን ግን ቅርሶቹ ወደየነበሩበት ይመለሱ የሚለዉ ሐሳብ የዋና ዋና መንግስታት እና ቤተ-መዘክሮችን ትኩረት እየሳበ ይመስላል።የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማንዌል ማክሮ ባለፈዉ ኅዳር «የአፍሪቃን ጥንታዊ ቅርሶች መጠበቅ «ቅድምያ የሚሰጠዉ ጉዳይ» ነዉ ማለታቸዉ ይታወሳል።
የምርጦች ምርጥ
በብሪታንያ ጦር ሠራዊት የተሰረቀው አብዛኛዉ የቅርስ መጠን አይታወቅም። በብሪታንያ ቤተ-መጻሕፍት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ውብ ጥንታዊ ፅሁፎች ይገኛሉ። "ምን እንደተፈፀም በሰፊው አይታወቅም" ያሉት ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያን 2017 ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ታዋቂዉ የታሪክ ምሁር ሪቻርድ ፓንክኸርስት «ወታደሮቹ ኢትዮጵያ የነበሯትን እና ያገኙትን እጅግ ዉብና ድንቅ የሆኑ የብራና ላይ ፅሑፎችና መጻሕፍትን ሁሉ መዉሰድ ችለዉ ነበር።» አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን የተወሰደዉን ዓይነት ጥራት እና ተፈላጊነት ያለዉ የብራና ፅሁፍ አይተዉ አያውቁም ነበር።"
ዓለም አቀፍ ጠባቂዎች
ጥንታዊ ቅርሶችን ወደ ነበሩበት ሃገራት እንዲመለሱ የሚደረገዉ ክርክር ጠንካራ ነዉ።ይሁንና ቅርሶቹ የሚገኙባቸዉ ቤተ-መዘክሮች ቅርሶቹን የመጠበቁን ኃላፊነት የኛ ነዉ የሚል ጠንካራ አቋም አላቸዉ። « ለሕዝብ እይታ ፤ ለምርምር እንዲሁም በቅርስ ጥበቃ ስብስብ ስር እንዲዉሉ በመላዉ ዓለም ለሚገኙ ምሁራን ምርምር ሥራ ክፍት እንዲሆኑ ይደረጋል» ሲሉ የብሪቲሽ ቤተ መጻሕፍት ባልደረባ ሉዊስ መኔኖይ ተናግርዋል።
ቅርሶችን ወደ አገራቸው መመለስ
ከመቅደላ የተዘረፈ አንድ የአንገት ሃብል በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ማስመለስ ተችሎአል። "በብሪታንያ ለቅርስ የሚደረገዉ ጥበቃ እና እንክብካቤ ከእኛ የተሻለ መሆኑ እሙን ነዉ፤ ነገር ግን ከመቅደላ ተዘርፈዉ ለተመለሱ ቅርሶች አዲስ አበባ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም የሚደረግላቸዉን ጥበቃና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማየት ይችላል» ሲሉ የኢትዮጵያ የመቅደላ ቅርሶች አስመላሽ ማኅበር (AFROMET)ተባባሪ መስራች ፕሮፊሰር አንድሪያስ እሸቴ ተናግረዋል።
የዲጂታል ቅጂዎች ሚና
የብራና ጽሑፎች እንዲመለሱ የሚከራከሩ ወገኖች እንደሚሉት አሁን ቅርሶቹ የሚገኙባቸዉ ቤተ-መጻሕፍት ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የዲጂታል ቅጂዎችን ሥለሚኖራቸዉ የሚያጡት ነገር ብዙም የለም። "የምንጠብቃቸዉ ቅርሶች በመላው ዓለም ተደራሽ ለማድረግ ዲጂታል ቴክኖሎጂን መጠቀም እንችላለን" ሲሉ ሜንጎኒ ተናግረዋል። ቤተ-መጽሐፍቱ ከኢትዮጵያ የተሰበሰቡ 250 ጽሑፎችን በዲጂታል ቅጂ ለማስቀመጥ አቅቅዷል።ከነዚሕ ዉስጥ 25ቱ-የዲጅታል ቅጂዎች በኢንተርኔት ተሰራጭቷል።
እርስን በተመለከተ በቤተ መጻሕፍት በኩል ያሉ ሕግጋት
ቅርሶቹ ወደ ዲጅታል ቅጂ ሲቀየሩ የሥነ-ጥበብ ስራዎቻቸዉ ይጎዳል። ብዙዎቹ በየሕዳጋቸዉ ብዙ ዝርዝር ማብራሪያ አላቸዉ።በዚሕም ምክንያት አጥኚዎች ከዲጅታሉ የማያገኙትን ለማግኘት እዚሕ ኢትዮጵያ የሚገኙትን ኦሪጂናሎቹን ማየት የሚፈልጉበት ብዙ ምክንያት አላቸዉ።» ሲሉ ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ ይናገራሉ።ይሁንና ቅርሶቹ የመመለስ-አለመመለሳቸዉ ዉሳኔ የቤተ-መዘክሮቹ አይደለም። የብሪታንያ ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ መወሰን አለበት።
የመፍትሔዎች ዓይነት
ቅርስን ለማስመለስ በሚደረገዉ ክርክር እንደሰወስተኛ አማራጭ የቀረበም ሐሳብ አለ። ቅርሶቹን ለጥንት ባለቤቶቹ ለረጅም ጊዜ ማዋስ የሚለዉ ነዉ። የቪክቶርያና አልበርት ቤተ-መዘክር ዳይሬክተር ትሪስትራም ሁንት እንደሚሉት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ለረጅም ጊዜ ዉሰት መስጠት የሚለዉን ሀሳብ አይቀበሉም።አሉላ ፓንክረስትም ይሕን ሐሳብ «በተገቢዉ መንገድ ለሟጓዝ ተገቢ እርምጃ።»ይሉታል።