የመቀሌዎች ዉዝግብ
ረቡዕ፣ ጥር 3 2009ማስታወቂያ
መቀሌ-ትግራይ በሚገኘዉ የንጉሠ-ነገሥት አፄ ዮሐንስ አራተኛ መታሰቢያ መሰናዶ ትምሕርት ቤት ሕንፃ ላይ የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ፎቶ ግራፍ መለጠፉ የከተማዋን ነዋሪዎች እያወዛገበ ነዉ።ተማሪዎች እና ወላጆች እንደሚሉት በትምሕርት ቤቱ ሕንፃ ላይ የመለስ ፎቶ ግራፍ የተለጠፈዉ የአፄ ዮሐንስን ታሪክ ለማንኳሰስ ነዉ።የትምሕርት ቤቱ ዳይሬክተር ግን ተቃራኒዉን ነዉ የሚሉት።ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ሌሎች ነዋሪዎች ደግሞ የመለስን ስምና ዝና ለማጉላት ሲባል መቀሌ ብቻ ሳይሆን በሌሎች አካባቢዎችም በሌሎች የታሪክ ሰዎች ስም የተሰየሙ ተቋማት በመለስ ስም እየተተኩ ነዉ ይላሉ።ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ