የመስቀል እና የደመራ በዓል
የደመራ በዓል በፍራንክፈርት ጀርመን
በጀርመን የሚኖሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የዘንድሮውን ፤ የ 2008 ዓ ም፣ የደመራ በዓል በፍራንክ ፈርት ጀርመን ደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስትያን በድምቀት አክብረዋል። በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እና በንግሥት እሌኒ ፍለጋ ተቆፍሮ፤ በኢየሩሳሌም የተገኘው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሠቀለበት መስቀል፣ የሚታሰብበት ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓል ነዉ።
የደመራ በዓል በፍራንክፈርት ጀርመን
የደመራ በዓል ሲከበር ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያዉያን የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል። የደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስትያን መዘምራን ክብረ በዓሉን በዝማሬ አድምቀዋል።
የደመራ በዓል በፍራንክፈርት ጀርመን
ኢትዮጵያዉያን እና ኤርትራዉያን ምዕመናን እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶችና የከተማዋ ነዋሪዎች በሥነ- ስርዓቱ ላይ ተገኝተዉ ነበር። እንደ ብዙዎች ግምት በዚህ ክብረ በዓል ከ1000 በላይ ሰዉ ነበር የተገኘዉ።
የደመራ በዓል በፍራንክፈርት ጀርመን
በደመራ በዓል ላይ ከተገኙት ምዕመናን በከፊል።
የደመራ በዓል በፍራንክፈርት ጀርመን
በፍራንክፈርቱ የደመራ በዓል ላይ ጀርመናዉያንን ጨምሮ የሌሎች ሀገራት ዜጎችም የክብረ በዓሉ ተካፋይ ነበሩ።
የደመራ በዓል በፍራንክፈርት ጀርመን
የደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስትያን መዘምራን ክብረ በዓሉን አድምቀዉት ነበር ያመሹት።
የደመራ በዓል በፍራንክፈርት ጀርመን
የደመራዉ ድምቀት የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ነበር።
የደመራ በዓል በፍራንክፈርት ጀርመን
በፍራንክፈርትና አካባቢዋ የሚኖሩ ምዕመን የደመራን በዓል ለማክበር ወደ ቦታዉ መትመም የጀመሩት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ነዉ።
የደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ
በገናዉም ለምሥጋና እና ለበዓሉ ድምቀት በአደባባዩ ታይቷል።
የደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ
ታዳሚዎችን ያሳተፈዉ ዝማሬ በኅብረት ሲቀርብ።
የደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ
በዓሉን ያደመቀዉ የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን ወረብ።
የደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ
የመስቀል በዓል በመላዉ ኢትዮጵያ በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በደምቀት ተከበረ። በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ነዉ የተከበረዉ።
የደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ
በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተካሄደዉ የደመራ በዓል ላይ።