የመስቀል በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ
ሐሙስ፣ ኅዳር 26 2006ማስታወቂያ
የኢትዮጵያውን የመስቀል በዓል አከባበር የተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት፥ የሳይንስ እና የባሕል ድርጅት UNESCO በዓለም ሕሊናዊ ቅርስነት መመዝገቡን አስታውቋል ። ባኩ-አዘርባጃን ዉስጥ በመካሄድ ላይ ባለው 8 ተኛው የዓለም ህልናዊ ባህላዊ ቅርሶች ጉባኤ ላይ የተለያዩ ሃገራት 30 ህሊናዊ ቅርሶች እንዲመዘገቡላቸው አቅርበው ነበር ። የመስቀል በዓል አከባባር በባለሞያዎች ተገምግሞ በዚህ ጉባኤ ተቀባይነት ካገኙት ህሊናዊ ቅርሶች አንዱ ነው ። ሃይማኖት ጥሩነህ ከፓሪስ ዝርዝሩን አዘጋጅታለች ።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ