የመራሒተ-መንግስት አንጌላ ሜርክል ውሳኔ እና የጀርመን ፖለቲከኞች አቀባበል
ሰኞ፣ ኅዳር 12 2009ማስታወቂያ
ለአስራ አንድ ዓመታት ጀርመንን የመሩት እና የካበተ ልምድ አላቸው የሚባልላቸው አንጌላ ሜርክል ከዚህ ውሳኔ ለመድረስ አብዝተው ማሰላሰላቸውን ተናግረዋል። አንጌላ ሜርክል በጎርጎሮሳዊው 2017 ዓ.ም የሚካሔደው ምርጫ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ቀላል እንደማይሆን በትናንትናው ዕለት ተናግረዋል። መራሒተ-መንግስቷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጉልህ እየታየ የመጣው ፅንፍ መያዝ አንዱ ፈተናቸው መሆኑን አልሸሸጉም። ለመሆኑ የመራሒተ-መንግስቷን በመጪው ምርጫ የመወዳደር እቅድ የጀርመን ፖለቲከኞች እንዴት ተቀበሉት? ኃሳባቸውንስ ለማሳካት የሚገጥሟቸው ፈተናዎች ምንድን ናቸው?
ይልማ ኃይለሚካኤል
እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ