የመምህራን ተቃውሞው
ማክሰኞ፣ መጋቢት 25 2004ማስታወቂያ
መንግሥት በቅርቡ ፤ ለመምህራን ያደረገውን የደመወዝ ደረጃ ማሻሻያ ጭማሪ ፣ እንከን አለበት በማለት በመላ ሀገሪቱ ፣አልፎ -አልፎ የተቃውሞ እርምጃ ሲወስዱ መሰንበታቸው ተመልክቷል። በትምህርት ቤቶች አስተዳደር የተጻፈባቸውን ከሥራ የማሰናበቻ ደብዳቤ ችላ ብለው በሥራ ገበታቸው ያልተገኙት፤ የተገኙትም ቢሆኑ ፤በመንግሥት ተደረገ የተባለውን የደመወዝ ጭማሪ በጥብቅ ይቃወማሉ ተብሏል። የፌደራሉ የትምህርት ሚንስትር ዛሬ እንደገለጹት፤ የትምህርት ቤቶች ሥራ አስኪያጆች፣ በመምህራን ላይ እየፈጸሙ ያሉትን ከሥራ የማባረርና ከደመወዝ የማድ ተግባር አቁመው የመማር ማስተማሩ ሂደት ሳይደናቀፍ ስለሚቀጥልበት ሁኔታ እንዲመክሩማሳሰባቸውን ታደሰ እንግዳው የላከልን ዘገባ ያስረዳል።
ታደሰ እንግዳው
ተክሌ የኋላ
ሸዋዬ ለገሰ