የሔሊኮፕተር አደጋ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 18 2011ማስታወቂያ
አዲስ አበባ ከመጋቢት መጀመሪያዉ የአዉሮፕላን አደጋ ሐዘንዋ በቅጡ ሳትፅናና ዛሬ ሌላ የሔሊኮብተር አደጋ አጋጥሟታል።ወደ ጂማ ለመብረር ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባዉ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ የተነሳችዉ ባለሁለት ሞተር የግል ኩባንያ ሔሊኮብተር ቦሌ ቡል ቡላ ስትደርስ መኖሪያ ቤቶች ላይ ወድቃለች።በሕይወትና አካል ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።ንብረት ግን፣ የአካባቢዉ ነዋሪዎች እንደሚሉት ግምቱ በዉል ያልታወቀ ጠፍቷል።
ሠለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ተስፋለም ወልደየስ