የሐይማኖት ዓለሙ ቀብር
ማክሰኞ፣ መስከረም 13 2007ማስታወቂያ
ኢትዮጵያዊዉ ፀሐፌ ተዉኔት፤አዘጋጅ፤ተዋኝና የቲያትር ጥብብ መምሕር ሐይማኖት ዓለሙ ዛሬ በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን ተቀበረ። ሐይማኖት አለሙ በተዋኝነት፤በአዘጋጅነትና በፀፌ ተዉኔትነት በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ዉጪ በተለይ ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በበርካታ ድራማዎች ተሳትፏል።ሐይማኖት በተለያዩ ቲያትሮች በሥራ-አስኪያጅነትና በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲም በመምሕርነት ያገለገለ የጥበበብ ሰዉ ነበር።68 ዓመቱ ነበር።ያረፈዉ ባለፈዉ እሁድ ነዉ።በቀብሩ ሥነ ሥርዓት ዘመድ-ወዳጆቹ፤ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የሐይማኖት መሪዎች ተገኝተዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር የቀብሩን ሥርዓቱን ተከታትሎት ነበር።
ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር
ነጋሽ መሐመድ