1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከሐረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው መንገድ መዘጋቱ

ዓርብ፣ ጥር 24 2011

የዞኑ ፖሊስ መመሪያ ሃላፊ መንገዱ፣መንግሥት መፍትሄ አልሰጠንም በሚሉ ተፈናቃዮች መዘጋቱን ተናግረዋል። መንገዱን ለማስከፈትም ከህብረተሰቡ ጋር የመነጋገር እቅድ እንዳለም ገልጸዋል። ከትናንት ምሽት አንስቶ መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት አሸከርካሪዎች እና መንገደኞች እየተጉላሉ መሆናቸውን DW ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎች አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/3Cagf
Äthiopien Stadt Jijiga
ምስል DW/T. Waldyes

ከሐረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው መንገድ መዘጋቱ

ከሐረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው መንገድ ሙሉ በሙሉ መዘጋቱን የምሥራቅ ሐረርጌ ፖሊስ አረጋገጠ DW ያነጋገገራቸው የዞኑ ፖሊስ መመሪያ ሃላፊ መንገዱ፣መንግሥት መፍትሄ አልሰጠንም በሚሉ ተፈናቃዮች መዘጋቱን ተናግረዋል። መንገዱን ለማስከፈትም ከህብረተሰቡ ጋር የመነጋገር እቅድ እንዳለም ገልጸዋል። ከትናንት ምሽት አንስቶ መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት አሸከርካሪዎች እና መንገደኞች እየተጉላሉ መሆናቸውን DW ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎች አስታውቀዋል። የድሬዳዋው  ወኪላችን መሳይ ተክሉ ዝርዝሩን ልኮልናል።
መሳይ ተክሉ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ