የሐረሪ መስተዳድር ሹም ሽር
ሐሙስ፣ ጥቅምት 29 2011ማስታወቂያ
የሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባደረገዉ አስቸኳይ ስብሰባ እስከ ዛሬ የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር የነበሩትን አቶ ሙራድ አብዱላሒን ሽሮ በምትካቸዉ አቶ ኦሪዲን በድሪን በርዕሠ-መስተዳድርነት ሾሟል።የቀድሞዉ ርዕሠ መስተዳድር ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡት ከአራት ወር በፊት ነበር።አዲሱ ርዕሠ መስተዳድር በክልሉ ለረጅም ዓመታት በተለያዩ ኃላፊነቶች ሲያገለግሉ ነበር። ጉዳዩን የተከታተለዉ የድሬዳዋዉ ጋዜጠኛ መሳይ ተክሉ እንደሚለዉ የአዲሱ ርዕሠ መስተዳድር መሾም የተወሳሰበዉን የሐረሪ መስተዳድር ችግር ለማቃለል ይረዳል የሚል ተስፋ አሳድሯል።
መሳይ ተክሉ
ነጋሽ መሐመድ
ተስፋዓለም ወልደየስ