የሆስፒታሉ አቅምና የታካሚዉ ብዛት
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 29 2011ማስታወቂያ
አዲስ አበባ ዉስጥ በ2001 የተመሠረተዉ የልብ ሕክምና ሆስፒታል ለበርካታ ሕሙማን በተለይም ለልጆችና ለሕፃናት ቀዶ-ሕክምናን ጨምሮ የተለያዩ የልብ ሕክምናዎችን እየሰጠ ነዉ።«የልብ ማዕከል ኢትዮጵያ» የተሰኘዉ ሆስፒታል ሕክምናዉን የሚሰጠዉ በነፃ ነዉ።ይሁንና ሆስፒታሉ እስካሁን ብዙዎችን ቢረዳም ሕክምና የሚያስፈልጋቸዉ ሕሙማን ቁጥር ከሆስፒታሉ ሐኪሞችና ቁሳቁስ ጋር ሲነፃፀር በጣም ከፍተኛ በመሆኑ በሺ የሚቆጠሩ ሕሙማን ለበርካታ ዓመታት ወረፋ ለመጠበቅ ይገደዳሉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ እንደዘገበዉ ወረፋ እየጠበቁ ሕይወታቸዉ የሚያልፍ ሕሙማን ቁጥርም ቀላል አይደለም።ሰለሞን ሆስፒታሉን ጎብኝቶ ለዛሬዉ ጤናና አካባቢ ተከታዩን ዝግጅት አጠናቅሮልናል።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ