የላሊበላ ዐብያተ ክርስቲያናት
ዓርብ፣ ጥር 24 2011ማስታወቂያ
የላሊበላ ውቅር ዐብያተ ክርስቲያናት የጥገና ሂደት እንዲፋጠን የከተማዋ አስተዳዳሪዎች እና ነዋሪዎች ጠየቁ። ነዋሪዎቹ የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር በቦታው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ለDW እንደተናገሩት ጥገናው በፍጥነት ካልተካሄደ አብያተ ክርስቲያናቱ ሊፈርሱ ይችላሉ የሚል ስጋት አለን ብለዋል። የከተማዋ ከንቲባ ለDW እንደተናገሩት ዐብያተ ክርስቲያናቱ ከዚህ ቀደም ሲደረግላቸው በነበረ ጥገና እና በተፈጥሮዊ ምክንያቶች ብዙ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከፕሬዝዳንት ሽታይንማየር ወደ ስፍራው ተጉዞ የነበረው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር በጉዳዩ ላይ የከተማዋን አስተዳዳሪዎች እና ነዋሪዎች አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ