የሊቢያ ፀጥታና አዲሱ መንግሥቷ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 9 2008ማስታወቂያ
በምዕራባዉያን መንግሥታት ድጋፍና ግፊት ለተመሠረተዉ ለአዲሱ የሊቢያ ጊዚያዊ ብሔራዊ አንድነት መንግሥት የጦር መሳሪያ እንደሚያስታጥቁ ዩናይትድ ስቴትስና ተባባሪዎችዋ አስታወቁ።ትናንት ቪየና-ኦስትሪያ ዉስጥ ሥለ ሊቢያ የተነጋገረዉ ሥብሰባ ሲያበቃ የዩናይትድ ስቴትሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር እንዳሉት ተሰብሳቢዎቹ አዲሱን የሊቢያ መንግሥት ለማስታጠቅና ለመርዳት ተስማምተዋል።በሊቢያ ላይ የተጣለዉ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ግን ገና አልተሰነሳም።በምዕራባዉያን መንግሥታት ጦር የተደገፉት የቀድሞዎቹ የሊቢያ አማፂያን የሐገሪቱን የረጅም ጊዜ መሪ ኮሎኔል ሙዓመር ጋዳፊን ከገደሉ ወዲሕ ሰሜን አፍሪቃዊቱ ሐብታም ሐገር የፍርስራሽ መከመሪያ እንደሆነች አምስተኛ ዓመቷ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ