1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የለገጣፎ ተፈናቃዮች እሮሮ

ረቡዕ፣ ግንቦት 28 2011

ከ4 ወራት በፊት ሕገወጥ ግንባታን ተከትሎ የተሠራ ነው በሚል ቤታቸው የፈረሰባቸው የለገጣፎ ከተማ ነዋሪዎች ወደጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በመሄድ አቤቱታ አቀረቡ። ወደ ውስጥ ተመርጠው መግባታቸውን የሚናገሩት የተፈናቃዮቹ ተወካዮች  መፍትሄውን ከኦሮሚያ ክልል ነው የምታገኙት የሚል ምላሽ በጽ/ቤቱ ቅሬታ ሰሚ አካል እንደተሰጣቸው ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3JuKV
Äthiopien Addis Abeba
ምስል DW/S. Muchie

«የመጪው ክረምት ዝናብ አሳስቧቸዋል»

  በርከት ያሉ ሰዎች ተጠልለው ከሚኖሩበት ቤተ ክርስቲያን ተነስተው ቢመጡም ተስፋ የሌለው ምላሽ እንደጠበቃቸው በተለይ እናቶች በምሬት መድረሻ አጣን በማለት ነው የሚገልፁት። ያልሄድንበት ቅሬታ ያሰማንበት ቦታ እና ባለስልጣን የለም የሚሉት እነዚህ ሰዎች ሀገሪቱ ተፈናቃዮችን እየመለሰች ነው እየተባለ እኛን ግን እስካሁን ድረስ ያየን ባለስልጣንና የመንግሥት አካል አለመኖሩ ተስፋ አስቆርጦናል ብለዋል። በምሬት ሲያለቅሱ የነበሩ እናቶች ህይወት እንደከበዳቸውና ምንም የሚታያቸው ተስፋ እንደሌለ መንግሥት ግን እንዲደርስላቸውና ከክረምቱ ዝናብ እንዲከላከላቸው ፣ በዘላቂነትም የነበራቸውን ህይወት እንዲመሩ እንዲያግዛቸው ተማጽነዋል። በስፍራው ተገኝቶ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ተከታዩን ልኮልናል። 

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ