የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሁለተኛ ዓመት፤20 መጋቢት 2005ዓርብ፣ መጋቢት 20 2005ከሱዳን ጋር ከሚያዋስነው ድንበር 40 ኪሎሜትር ርቀት ባለው ቦታ፣ በጥቁር ዐባይ ላይ በመገንባት ላይ ያለው፣ በአፍሪቃ በታላቅነቱ ወደር እንደማይኖረው የሚነገርለት ግድብ ፣ግንባታው ሲፈጸም 5,250 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያመነጭ መገለጡ የሚታወስ ነው።https://p.dw.com/p/1870cምስል CC/Mark Abelማስታወቂያ ይኸው ትልቅ ግድብ ፣ ሥራው የተጀመረበት ሁለተኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ መሆኑን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የላከልን ዘገባ ያስረዳል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ፤ ከወላይታ በኩል ከፍላጎታችን ውጭ ፤ ለግድቡ ሥራ ከደመወዛችን እንዲቆረጥ እየተደረገ ነው ሲሉ ያማረሩ ወገኖችን ቅሬታም ዘገባው አካቷል። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተክሌ የኋላ ነጋሽ መሐመድ