የህክምና ተማሪነት በጀርመን
ዓርብ፣ መስከረም 25 2005ማስታወቂያ
እስቲ ስንቶቻችን ነን ፤ ትልቅ ስትሆኚ ወይንም ስትሆን ምን መሆን ትፈልጋላችሁ ስንባል፤ ዶክተር፣ ፓይለት ወይንም ሳይንቲስት ያልን። በርግጥ በልጅነት ያልነው እና አሁን ለመማር የምንፈልገው ወይንም የተማርነው ያኔ ያልነው ነውን? የዛሬው እንግዳችን- ሰብለወንጌል የመኔ -የልጅነት ምኞቷን እየተማረች ነው። የህክምና ትምህርትን።
የህክምና ትምህርት ቢያንስ ስድስት ዓመት ተኩል ይፈጃል። በዚህ ረዥም የትምህርት ጊዜዋ ሰብለወንጌል የገጠሟትን ፈተናዎች አጫውታናለች።
ከጀርመን ሀገር ወደ ጎንደር ሄዳ በአሁኑ ሰዓት የስራ ልምምድ በማድረግ ላይ ያለችው የህክምና የመጨረሻ አመት ተማሪ -ሰብለወንጌል በጎንደር በተወሰኑ እና ዘመናዊ ባልሆኑ መሳሪያዎች መስራትን እንዴት ለመደችው? በምኞት ደረጃ የህክምና ትምህርትን ለመከታተል ለሚጥሩ ወይንም በመማር ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንስ ሰብለወንጌል ምን ታካፍላለች? ከዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
ነጋሽ መሐመድ