የህንጻ ጥበበኞች
ዓርብ፣ ጥር 24 2011ማስታወቂያ
አርክቴክቸር በአማርኛው ኪነ ህንፃ የሚል ትርጓሜ አለው። ህንጻ የመገንባት ጥበብ እንደማለት ነው።
ኪነ-ህንፃ በውበቱና በጥንካሬው ከሚመዘንባቸው ዋነኛውና መሰረታዊ መስፈርት ሆኖ በብዙዎች ዘንድ ይቀመጣል። በአለማችን እጅግ ለእይታ ውብና ሰማይ ጠቀስ የሚሏቸው ረጃጅም ህንጻዎች ተገንብተዋል። ህንፃ ተደረመሰ ብለው ከሚሰሙት ዜና በዘለለ፤ ዘመናዊነቱን የህንጻ ኪነ ጥበብም ያደንቃሉ። የህንጻ ባለሙያዎቹ ለጥንካሬው ይጨነቃል ያሉናል የዛሬ እንግዶቼ ዮሀንስ ካሳ እና ያሚን አሚን፤ በሙያቸው አርቴክቸሮች ወይም የኪነ ህንጻ ባለሙያዎች ናቸው። በ2002 ከመቀሌ ዩኒበርስቲ በአርቴክቸር እና ኤርባን ፕላንግ ተመርቀዋል። የጓደኝነት ጥምረታቸው የሚጀምረው በዩኒበርስቲ ቆይታቸው ጀምሮ ነው። የኪነ-ህንጻ ባለሙያ አብዛኛው ስራው የህንጻው ዲዛይን ላይ ያተኮረ ቢሆንም፤ የግንባታ ኢንዱስትሪውን በዋናነት ይመራል ሲል ዮሀንስ ይገልጻል። ከሀሳብ ጅማሮ የግንባታ ቦታ መረጣ እስከ ህንጻው አልቆ አገልግሎት እስከሚሰጥበት ጊዜ ድረስ፤ የኪነ ህንጻው ባለሙያ ስራ ነው ይለናል። ከወጣት የህንጻ ባለሙያዎቹ ጋር የነበረንን ቆይታ ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ።