ሕግ እና ፍትሕ
የሁለቱ የዋልድባ ገዳም መነኮሳት የፍርድ ቤት ውሎ
ሰኞ፣ መጋቢት 10 2010ማስታወቂያ
ብይኑን የሰጠው አባ ገብረሥላሤ እና አባ ገብረየሱስ የተባሉት ተከሳሾች ጠበቃ የማረሚያ ቤቱን ርምጃ በመቃወም ያቀረበውን አቤቱታ በዛሬው ዕለት ያዳመጠው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ የወንጀል ችሎት ልደታ ምድብ ነው። ከወትሮዉ በተለየ በዛሬዉ ዕለት የመነኮሳቱን የፍርድ ቤት ዉሎ ለመከታተል ቁጥሩ በርከት ያለ ሕዝብ በስፍራዉ ተገኝቷል። ዛሬ የተሰየሙት አዳዲስ ዳኞች ሲሆኑ ፍርድ ቤቱ በቀጣይ መነኮሳቱ ላይ የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለመጋቢት 18 ቀን 2010ዓ,ም ቀጠሮ መስጠቱንም ለመረዳት ተችሏል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ