1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሀዋሳ ሀይቅ የተደቀነበት ስጋት

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 7 2003

ሀምሳኛ ዓመቷን በቅርቡ ያከበረችው የሀዋሳ ከተማ ስሟን ያገኘችበት፤ ለመቆርቆርም ያበቃት አጠገቧ ተንጣሎ የሚገኘው ሀይቅ ነው- የሀዋሳ ሀይቅ።

https://p.dw.com/p/QdPT
ምስል AP GraphicsBank/DW

በየጊዜው የብክለት አደጋ እየገጠመው እንዳለ ይነገራል።

በተለይም በአከባቢው ከሚገኙ ግንባታዎችና የአገልግሎት መስጪያ ተቋማት ጋር በተያያዘ የሀዋሳ ሀይቅ ስጋቶች ተደቅነውበታል ይላሉ የአከባቢ ተቆርቋሪዎች። በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የባዮሎጂ መምህር የሆኑት ዶክተር ግርማ ጥላሁን በሀዋሳ ሀይቅ ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶችን አቅርበዋል። የሀዋሳ ሀይቅ አደጋ ውስጥ ነው ይላሉ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የባህልና ቱሪዝም የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አዲሴ አኒቶ ስጋቱ እንዳለ ይገልጻሉ። በሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተገነቡ ያሉ ትልልቅ ሆቴሎች ለሀይቁ ስጋት ወይስ ደህንነት? በእርግጥ የአከባቢ ተቆርቋሪዎች ደህንነት ስለመሆኑ ይጠራጠራሉ። የከተማዋ የባህልና ቱሪዝም አቶ አዲሴ አኒቶ ስጋት ናቸው ማለቱን ባይቀበሉትም ችግሮች እንዳሉ ግን አልደበቁም።

መሳይ መኮንን
ሒሩት መለሰ