1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሀረሪ ክልል ፖሊስ የተሀድሶ ስልጠና

ዓርብ፣ መጋቢት 6 2011

የክልሉ ፖሊስ ሥልጠና በሚወስደበት ወቅትም የክልሉን ሰላምና ፀጥታ የማስጠበቁን ሥራ የመከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ በጋራ ተክተው እንደሚሰሩ ተገልጿል። የክልሉ ፖሊስ ኃይል በአድሎአዊነት እና የህግ የበላይነትን ባለማስክበር ሲወቀስ ቆይቷል።

https://p.dw.com/p/3Ey93
Stadtmauer von Harar Stadt im Südosten von Äthiopien
ምስል Azeb Tadesse Hahn

የሀረሪ ክልል ፖሊስ በሙሉ የተሀድሶ ስልጠና ሊወስድ ነው

የሐረሪ ክልል ፖሊሶች በሙሉ የተሀድሶ ስልጠና ሊወስዱ ነው። ሥልጠናው በሁለት ዘርፎች ተከፍሎ ለአንድ ወር የሚሰጥ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለDW አስታውቋል። የክልሉ ፖሊስ ሥልጠና በሚወስደበት ወቅትም የክልሉን ሰላምና ፀጥታ የማስጠበቁን ሥራ የመከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ በጋራ ተክተው እንደሚሰሩ ተገልጿል። የክልሉ ፖሊስ ኃይል በአድሎአዊነት እና የህግ የበላይነትን ባለማስክበር ሲወቀስ ቆይቷል። የድሬዳዋው ወኪላችን  መሳይ ተክሉ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
መሳይ ተክሉ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ