ዞን ዘጠኞች ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 21 2009ማስታወቂያ
ዛሬ ያስቻለው የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዞን ዘጠኝ በመባል የሚጠራው የድረ ገፅ ፀሀፍት ቡድን አባላት ላይ አቃቤ ህግ ላቀረበው ይግባኝ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ ። ፍርድ ቤቱ ዛሬ ብይን ይሰጣል ተብሎ ተጠብቆ ነበር ። ይሁን እና የስር ፍርድ ቤት ለሰጠው ፍርድ መሠረት የሆኑ የሲዲ እና የሰነድ ማስረጃዎች አላገኘንም በሚል ብይኑን አስተላልፏል ። ከዞን ዘጠኝ አባላት አንዱ ለዶቼቬለ እንደተናገረው ፍርድ ቤቱ ቤቱ አልደረሰኝም ካላቸው መረጃዎች አንዱ ሀገር ውስጥ የሚገኙትን የዞን ዘጠኝ አባላት አይመለከትም ። ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ