ዝክረ ቅዱስ ያሬድ
ሐሙስ፣ ግንቦት 22 2011ማስታወቂያ
ከዛሬ 1500 ዓመታት በፊት አክሱም ላይ የተወለደው ቅዱስ ያሬድ፣ በኪነጥበቡ ዘርፍ የዜማ ፈጣሪ፣ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ባለቅኔ እና ገጣሚ፤ በመንፈሳዊው ረገድ ደግሞ ጻዲቅ፣ መናኝ፣ ሰማዕት እና ለሃይማኖቱም ከፍተኛ በረከት ያቀረበ እንደሆነ ምሁራን ይናገሩለታል። ስለያሬዳዊ ዝማሬ ሲነሳ፣ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዕለት ከዕለት መንፈሳዊ አገልግሎት ያበረከታቸው የግዕዝ ፣ ዕዝል እና አራራይ ዜማዎች በየዕለቱ በቅዳሴ፣ በማኅሌት እና ሰዓታቱ አምልኮታዊ ሥርዓቱን ያደምቃል። እንዲህም ሆኖ ግን ቅዱስ ያሬድ ያበርክቶውን ያህል ዝናውን እንዳልገነነለት የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ይናገራሉ። ስለሥራዎቹ ብዙም በውጭው ዓለም ባለመታወቁም የእርሱ ቅኔዎች ላይ ምርምር ያካሄዱ አንዳንድ የውጭ ምሁራን እንዲህ ያለው የረቀቀ የጥበብ አስተሳሰብ ከኢትዮጵያ ሊሆን አይችልም ማለታቸውንም በጥናታቸው ለማሳየት ሞክረዋል። ይህን በመጥቀስም ስለቅዱስ ያሬድ ገና ብዙ መናገር እና ማስተማር እንደሚገባ ያሳስባሉ። በቅርቡ እዚህ በጀርመን ሀገር ቅዱስ ያሬድን ያዘከረ ጥናታዊ ጽሑፎችም የቀረቡበት መርሃግብር ተከናውኗል። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ፤
እንዳልካቸው ፈቃደ
ሸዋዬ ለገሠ