1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምባብዌና የአውሮፓው ሕብረት፣

ሐሙስ፣ የካቲት 13 2006

የአውሮፓውሕብረት፣በዝብምባብዌላይጥሎትየነበረውንማዕቀብበአብዛኛውእንዲነሣአድርጓል።ከፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤና ባልተቤታቸውበስተቀር ፰ የመንግሥትአባላትየሆኑፖለቲከኞችወደአውሮፓውሕብረትአባልሃገራት መግባትይፈቀድላቸዋልተብሏል።የአውሮፓው ሕብረት በዝምባባዌ ላይ ማዕቀብ

https://p.dw.com/p/1BD0c
ምስል Getty Images/Afp/Alexander Joe

Morgan Tsvangirai
ምስል JEKESAI NJIKIZANA/AFP/Getty Images

የጣለው፤ እ ጎ አ በ 2002 ዓ ም በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ፤ ሙጋቤ ውጤቱ እንዲጭበረበርና ለእርሳቸውና ለገዥው ZANU-PF ፓርቲአቸው እንዲመቻች አድርገዋል በማለት ነው።

በዝምባብዌ ፣የፍትሕናየሰብአዊመብትአስጠባቂ፣ፕሬዚዳንቱነው።እነዚህከተሣኩ፣የአውሮፓውሕብረትቃል

አቀባይሴባስቲያንብራባንትለዶቸቨለእንዳሉትጠቅላላውማዕቀብየሚነሣበትማለፊያአጋጣሚ

ይፈጠራልማለትነው።የዝምባብዌውገዥፓርቲዛኑፒኤፍቃልአቀባይሩጋሬጋምቦበፕሬዚዳንትሮብት

ሙጋቤላይየተጣለውእገዳአለመነሣቱበፍፁምተቀባይነትየለውምባይናቸው።

የዝምባባዌ መንግሥት፣ የተሸራረፈ ሳይሆን፤ ከእነአካቴው ማዕቀቡ እንዲወገድ ነው የጠየቀው። የቀድሞይቱ የብሪታንያ ቅኝ ግዛት ሮዴሺያ፤ ዝምባብዌ፣ እ ጎ አ በ 1980 ነጻነቷን ከተቀዳጀችበት ጊዜ አንስቶ የሚያስተዳድሯት አንድ ርእሰ-ብሔር ፤ ሮበርት ሙጋቤ ናቸው። የአውሮፓው ኅብረት የውጭ ፖለቲካ ጉዳይ ኀላፊ ካትሪን ኤሽተን እንደሚሉት ፤ዓምና ከመጋቢት ወር አንስቶ፤ በዝምባባዌ የውስጥ ፖለቲካ የመሻሻል ምልክቶች በመታየት ላይ ናቸው። በመሆኑም ከ 100 በላይ በሚሆኑ ግለሰቦችና ኩባንያዎች ላይ የአውሮፓው ሕብረት አገዳ ማንሳቱን ነው የጠቆመው። የአውሮፓው ሕብረት ኮሚሽን ቃል አቀባይ ሴባስቲያን ብራባንት---
«ዝምባብዌውስጥ፣በመንግሥትእጅግከፍተኛውሥልጣንያለውርእሰ-ብሔሩ፣ሕገ-መንግሥቱ በሥራእንዲተረጎምየማድረግኀላፊነትአለበት።የዴሞክራሲሥርዓቶችና

የሕግየበላይነትእንዲከበርማድረግምሥራውነው።እነዚህእርምጃዎችእስከተወሰዱድረስየአውሮፓው

ሕብረትማዕቀቡንማንሣትየሚችልበትማለፊያትልምአለ»።

በሥልጣን ላይ የሚገኘው «ዛኑ ፒ ኤፍ » ቃል አቀባይ የዝምባብዌውን ፕሬዚዳንት ማዕቀብ ከሚነሳላቸው ወገኖች ሥም ዝርዝር አለመጨመሩ ፍጹም ተቀባይነት አይኖረውም። አገዳው እንደእኝህ ባለሥልጣን አባባል ፤ በአንድ ሰው ላይ ብቻ የተወሰደ አይደለም።

«የተባለውምንድንነው?ማዕቀብበሳቸውላይእስከፀናድረስእገዳውባገሪቱበመላ
እንደተጣለይቆያልማለትነው።»

Wirtschaft in Simbabwe
ምስል DESMOND KWANDE/AFP/Getty Images

በፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤና በባልተቤታቸው ወ/ሮ ግሬስ ሙጋቤ ላይ ማዕቀቡ ይቀጥላል በመባሉ፤ ሙጋቤ ይህን አያያዝም ሆነ አቋም ለራሳቸው ፖለቲካ መጠቀሚያ ሳያደርጉት አይቀሩም። በሃምበርግ የአፍሪቃ ጉዳዮች የምርምር ተቋም ባልደረባ ዩልያ ግራውፎግል-
፫«መንግሥትይህንእገዳለራሱፖለቲካእንዲያመችአድርጎነውየተጠቀመበት።እገዳውንየፈለገው

የተቃውሞውወገን፣ሕዝቡበኤኮኖሚእገዳ እንዲጎዳ፣ እንዲሠቃይ
የሚሻ ነውተብሎነውየተነቀፈው።»

የአውሮፓው ሕብረት ኮሚሽን ቃል አቀባይ ሴባስቲያን ብራባንት በበኩላቸው እንዲህ ነበረ ያሉት--
፬« እዚህላይማገናዘብየምንችለውምንድንነው፣እነዚህእርምጃዎችበዝምባብዌሕዝብላይቀጥተኛ፣

የኤኮኖሚውም፣ሆነየማሕበራዊተፅእኖእንደሌላቸውነው።ስለዚህበሰፊውለደረሰውማሕበራዊና

ኤኮኖሚያዊተግዳሮት ልንወቀስአይገባም።»

ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤና ባልተቤታቸው በአውሮፓው ሕብረት ዘንድ አይፈቀዱም ይባል እንጂ በመጋቢታ ወር ማለቂያ ገደማ ወደ ብራሰልስ ብቅ ማለታቸውና በክብር አቀባበል ሳያደረግላቸው አንደማይቀር ነው በመነገር ላይ ያለው። ያኔ የአውሮፓው ሕብረትና የአፍሪቃ ሃገራት መራኅያነ-መንግሥትና ርእሳነ ብሔር ጉባዔ ይካሄዳል። በአንዲህ ዓይነቱ ዓለም አቀፍ ጉባዔ አስተናጋጂዋ ሀገር ቤልጅግ ፤ ለሙጋቤ የመግቢያ ፈቀድ መስጠት ይጠበቅባታል። ሙጋቤ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ጉባዔ፣ እ ጎ አ በ 2007 በሊዝበን፤ ፖርቱጋል፤ እንዲሁም በ 2010 ፤ በትሪፖሊ ፤ ሊቢያ መሳተፋቸው አይዘነጋም። በሊዝበኑ ጉባዔ ፤ ራሳቸውን ያገለሉ የያኔው የብሪታንያ ጠ/ሚንስትር ጎርደን ብራውን ነበሩ።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ