1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዚምባብዌ ና የአልማዝ ማዕድኗ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 4 2005

ድርጅቱ ተሰርቋል ያለው ገንዘብ ለዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ፓርቲ ዛኑ ፒፍ ባለሥልጣናትና ለደላላሎች መበልጸጊያ ነው የዋለው ። መንግሥት ግን ክሱን ሃሰት ና በምዕራባውያን የተፈበረከ ሲል አጣጥሎታል ።

https://p.dw.com/p/16iiT
Zimbabwe, International Diamond Conference: Präsident Robert Mugabe (Zimbabwe) and ehemaliger Präsident von Südafrika, Thabo Mbeki. Copyright: DW/Columbus Mavhunga 12 und 13.11. 2012
ምስል DW

የአልማዝ ማዕድን በብዛት ከሚመረትባት ከዚምባብዊ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ አልማዝ ተስርቋል ሲል አንድ የአልማዝ ንግድ ታዛቢ ድርጅት አስታወቀ ። እንደ ድርጅቱ ተሰርቋል ያለው ገንዘብ ለዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ፓርቲ ዛኑ ፒፍ ባለሥልጣናትና ለደላላሎች መበልጸጊያ ነው የዋለው ። መንግሥት ግን ክሱን ሃሰት ና በምዕራባውያን የተፈበረከ ሲል አጣጥሎታል ። የዶቼቬለ የዚምባብዌ ዘጋቢ ኮምቡስ ማቭሁንጋ የዘገበውን ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።ፓርትነርሽፕ አፍሪቃ ካናዳ በተባለው የአልማዝ ንግድ ታዛቢ ድርጅት ትናንት ባወጣው ዘገባ የዚምባብዌአልማዝ ለሃገሪቱ ሳይሆን ለከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት መበልፀጊያ መዋሉን ይጠቁማል ። የዚምባብዌ የማዕድንንና ልማት ኮርፖሬሽን ሃላፊ ጉድ ዊል ማሲሚሬምብዋ ግን ዘገባውን አጣጥለው ምዕራባውያን የፈበረኩት ወሪ ነው በለዋል ። ሃላፊው ዘገባው የወጣበትን ጊዜ ራሱ አጠያያቂ ነው ይላሉ ።

Miners dig for diamonds in Marange, Zimbabwe, Wednesday, Nov. 1, 2006. Police in Zimbabwe arrested 16,290 illegal miners, mostly gold panners, in a countrywide blitz that began just over a month ago, the official media reported Thursday, Dec. 28, 2006. (AP Photo/Tsvangirayi Mukwazhi)
ምስል AP

በርሳቸው አባባል ይህ ዘገባ የወጣው ዚምባብዌ ገፅታዋን ለማስተካከል በአልማዝ ማዕድን ንግድ ላይ የሚነጋገር ጉባኤ በምታስተንግድበት ወቅት ነው ። ማሲሚሬምብዋ በዘገባው ላይ አስተያየት ከመስጠት ይልቅ የዚምባብዊ አልማዝ በአለም ገበያ ትክክለኛውን ዋጋ እንዲያገኝ ምዕራባውያን በሃገሪቱ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ማንሳት ይኖርባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል ። እጎአ በ2ሺህ አመተ ምህረት ዚምባብዌ ሰብአዊ መብት እንደምትጥስ ዘገባ ከቀረበ በኋላ ምዕራባውያን በዚምባብዌው ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ና በከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው ላይ የተመረጡ ማዕቀቦች ጥለውባቸዋል ። በሃገሪቱ የሚካሄደው የሰብአዊ መብት ጥሰት ወደ ሃገሪቱ የማዕድን ማውጫዎችም በመዛመቱ የአለም የአልማዝ ንግድን የሚቆጣጠረው ኪምብርሊ ፕሮሰስ ዚምባብዌን ከአልማዝ ንግድ ገበያ ለማገድ አስገድዶታል ። ይህ እገዳ ግን ተነስቷል ። ያማለት ግን የአውሮፓ ህብረት በዚምባብዌ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ያነሳል ማለት እንዳይደለ በዚምባብዌ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር አልዶ ዴል አሪካ ተናግረዋል

Zimbabwean Prime Minster Morgan Tsvangirai, center, chats to Mines and Minerals Minister, Orbert Mpofu, left and Zanu PF Chairman, Simon Khaya Moyo, right, following the granting of a Kimberley Process certificate to Zimbabwe in Harare, Wednesday, Aug. 11, 2010. Zimbabwe began selling millions of carats of rough diamonds Wednesday that were mined from an area where human rights groups say soldiers killed 200 people, raped women and forced children into hard labor. Abbey Chikane, Zimbabwe monitor of the world diamond control body, certified the diamonds ready for sale on Wednesday, having said controversy-plagued diamonds from eastern Zimbabwe met minimum international standards. (AP Photo/Tsvangirayi Mukwazhi)
ምስል AP

ብራሰልስና ሃራሬ ግንኙነታቸውን ወደ ቀድሞው ሁኔታ ለመመለስ የሚያካሂዱት ንግግር ዚምባብዌ እንደምትለው በአውሮፓ የአልማዝ ገበያ ዋጋ ላይ የፅእኖ እያሳደረ ነው ። ከአለም ከፍተኛ የአልማዝ ክምችት የሚገኝባቸው የዚምባብዌ የአልማዝ ማዕድን ማውጫዎች የሃገሬቱን ኤኮኖሚ ከሚገኝበት አዘቅት እንዲወጣ አላገዙም አንዳንዶች የችግሩ ምክንያት ሙስና ነው ይላሉ ። ሙጋቤ ደግሞ ምክንያቱ ማዕቀቡ ነው ይላሉ ። በዚህ መነሻ ነው መንግሥት ለችግሩ መፍትሄ ፍለጋ የ 2 ቀናት ጉባዜ ያዘጋጀው ። በዚሁ ጉባኤ ላይም ዓለም አቀፍ ደላሎችና ከአልማዝ አምራች ሃገራት የተውጣጡ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል ። ሻሚሶ ሚትሶ የተባሉት የዚምባብዌ የሲቪል ማህበራት ጥምረት መሪ እንዳሉት ጉባኤው በሰዎች ችግሮች ላያ ካላተኮረ ለርሳቸው ትርጉም አይኖረውም ።

ኮሎምቡስ ማቭሁንጋ

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ