ዚምባብዌና የዘገየው የምርጫ ውጤት23 መጋቢት 2000ማክሰኞ፣ መጋቢት 23 2000በዚምባባዌ ምክር ቤታዊውና ፕሬዚደንታዊው ምርጫ ከተካሄደ ዛሬ ሶስተኛ ቀን ሆኖታል። ሆኖም፡ የምርጫው ይፋ ውጤት እስካሁን ገና አልወጣም። ይህም ገዢው የዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ውጤቱን ለማጭበርበር ያደረገው ነው የተቃውሞ ወገኖች ወቀሳ እያሰሙ ነው። የሀገሪቱ የአስመራጭ ኮሚሽን ህዝቡ ውጤቱን በትዕግስት እንዲጠብቅ ጥሪ ባቀረበበት ባሁኑ ጊዜ፡ የተቃውሞው ወገንና የውጭ መንግስታት ኮሚሽኑ ውጤቱን በተቻለ ፍጥነት እንዲያወጡ እያሳሰቡ ነው።https://p.dw.com/p/E0ZAየተቃውሞው ወገን ደጋፊዎችምስል APማስታወቂያ