1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተሽከርካሪዎች ዘረፋ

ረቡዕ፣ ሰኔ 5 2011

አቤት ባዮቹ እንደሚሉት በየከሞቹ መኪኖችን እያስቆሙ መንገደኞችና አሽከርካሪዎችን ወይም ረዳቶቻቸዉን እያስፈራሩ አንዳዴም እየደበደቡ ገንዘብ የሚቀበሉ ወጣቶች «ሃይ ባይ» አላገኙም።የምሥራቅ ሐረርጌ ፖሊስ ግን ዘራፊዎችን እየተቆጣጠርን ነዉ ባይ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3KID2
Äthiopien East Harerghe
ምስል DW/M. Teklu

ዘረፋ በምስራቅ ኢትዮጵያ

 ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ወደ ምሥራቅ ኢትዮጵያና በተቃራኒዉ የሚጓዙ መንገደኞችና አሽከርካሪዎች የሚፈፀምባቸዉ ዘረፋና ድብደባ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ መምጣቱን አስታወቁ። መንገደኞች፣ አሽከርካሪዎችና ረዳቶቻቸዉ እንደሚሉት በተለይ ምሥራቅ ሐረርጌ የሚገኙ አነስተኛ ከተሞችን ገንዘብ ሳይከፍሉ አቋርጦ ማለፍ አይቻልም። አቤት ባዮቹ እንደሚሉት በየከሞቹ መኪኖችን እያስቆሙ መንገደኞችና አሽከርካሪዎችን ወይም ረዳቶቻቸዉን እያስፈራሩ አንዳዴም እየደበደቡ ገንዘብ የሚቀበሉ ወጣቶች «ሃይ ባይ» አላገኙም። የምሥራቅ ሐረርጌ ፖሊስ ግን ዘራፊዎችን እየተቆጣጠርን ነዉ ባይ ነዉ።

መሳይ ተክሉ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ