ዘረኝነት ቦታ የለዉም!
ዓርብ፣ ነሐሴ 22 2001ማስታወቂያ
ባንጻሩ ስፖርተኛይቱ የወርቅ ሜዳሊያዋን ይዛ አገሩዋ ስትገባ የደቡብ አፍሪቃዉ የስፖርት ፊደሪሽን ጉዳዩን የዘረኝነት ሁኔታ ነዉ እንጂ የተጠቀሰዉ ነገር ትክክል አይደለም ሲል ወቀሳዉን ወደ ጀርመን አሰምተዋል። ሁኔታዉ ወደ ዘረኝነት ፊቱን መለወጡ ያሳዘናቸዉ እስፖርተኛዋ ምርመራዉን እንድታካሂድ ያዘዘዉ የዉድድሩ አዘጋጅ የአለም አቀፍ የአትሊቲክስ ፊዲሪሽን ማህበር ዋና ሃላፊ አፍሪቃዊ ትዉልድ ያለዉ ነዉ፤ በተጨማሪ ምርመራ እንድታካሂድ መታዘዙ ያለ ጉዳይ ነዉ ሲሉ ዉንጀላዉን አጣጥለዉታል። በዚህ ጉዳይ ዙርያ የዶቸ ቤለዉ ሉድገር ሻዶምስኪ ሃተታ ጽፎአል ይልማ ሃይለሚካኤል እንዲህ ተርጉሞታል።
ይልማ ሃይለሚካኤል፣ አዜብ ታደሰ፣
ሂሩት መለሰ