ዘረኝነት -በፕሪቶርያ የቀሰቀሰው ተቃውሞ27 ነሐሴ 2008ዓርብ፣ ነሐሴ 27 2008በደቡብ አፍሪቃ መዲና ፕሪቶርያ በሚገኝ አንድ የልጃገረዶች 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ ጥቁር ደቡብ አፍሪቃውያት በተቋሙ ዘረኛ ፖሊሲ አንፃር ተቃውሟቸውን አሰሙ። ትምህርት ቤቱ ተማሪዎቹ ፀጉራቸውን በማጎፈር ፈንታ እንዲያለሰልሱ፣ እንዲሁም፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዳይናገሩ፣ ካለበለዚያ እንደሚታገዱ ያወጣው ደንብ ብርቁ ተቃውሞ ቀስቅሶዋል።https://p.dw.com/p/1Juytምስል imago/imagebrokerማስታወቂያ[No title]To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 audio በደቡብ አፍሪቃ የዘር አድልዎ መርህ ካበቃ ከሁለት አሰርተ ዓመት በላይ ወዲህ ትምህርት ቤቱ አሁን በጥቁሮቹ ተማሪዎቹ ላይ እየፈፀመ ያለውን የአድልዎ አሰራር እንዲያግድ የከተማይቱ እና የሀገሪቱ ባለስልጣናት አዘዋል። መላኩ አየለ አርያም ተክሌ አዜብ ታደሰ