ዓለም ዓቀፍ የኒዩክልየር ደህንነት ጉባኤ
ዓርብ፣ መጋቢት 23 2008ማስታወቂያ
ዋሽንግተን ዲሲ ዩናይትድ ስቴትስ ትናንት የተጀመረው 4 ተኛ ዓለም ዓቀፍ የኒዩክልየር ደህንነት ጉባኤ የኒዩክልየር ጦር መሣሪያ እና የምርቱ ግብዓቶች ጥበቃ ላይ ተነጋገረ ። ጉባኤው በተለይ በኒዩክልየር ጣቢያዎች ላይ ጥቃት እንዳይደርስ እንዲሁም የኒዩክልየር ምርት ግብዓቶች ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ እንደሚጠራው ቡድን ባሉ አሸባሪ ድርጅቶች እጅ እንዳይገቡ መወሰድ በሚገባቸው ጥንቃቄዎች ላይ መክሯል ። ዛሬ ያበቃል ተብሎ በሚጠበቀው በዚሁ ጉባኤ ላይ ከ5o በላይ የሃገራት መሪዎች ተካፍለዋል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ልኮልናል ።
መክብብ ሸዋ
ሒሩት መለሠ
አርያም ተክሌ