ዓለም አቀፍ የደህንነት ጉባኤ በጀርመን ሙኒክ
ዓርብ፣ ጥር 29 2001ማስታወቂያ
አዲሱ የUS አሜሪካ አስተዳደር፤ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲን አስመልክቶ ያዘጋጀውን ዕቅድ የመጀመሪያ ማብራሪያ በጀርመን ሙኒክ ዓመታዊ የደህንነት ጉባኤ ላይ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። አርባ አምስተኛው ዓመታዊ የደህንነት ጉባኤ ዛሬ ከምሽቱ አንድ ሠአት ላይ በጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሽታይንማየር ንግግር ተከፍቶ እስከ ፊታችን እሁድ ይዘልቃል። ኢራን፣ አፍጋኒስታን፣ አቶሚክ ሀይልና ሞስኮ ዋና የመነጋገሪያ አጀንዳ ይሆናሉ።