ዓለም አቀፉ የካቶሊካዉያን ጳጳሳት ጉባዔ
ሰኞ፣ የካቲት 18 2011ማስታወቂያ
ጉባዔዉ በተለያዩ የዓለም ሃገራት ዉስጥ በሚገኙ የካቶሊካዊት አብያተ ክርስትያናት ዉስጥ በልጆች እና በአዋቂዎች ላይ የተፈፀሙና የሚፈፀሙ የወሲብ ጥቃትና ትንኮሳን በግልጽ ለማዉጣትና ለመግታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ተወያይቷል። ትናንት ያበቃዉን የቫቲካኑን ጉባዔ የመሩት የካቶሊካዊት ቤተ-ክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ- ጳጳሳት ፍራንሲስ በበኩላቸዉ ስለ ችግሩ በግልፅ መወያየት እንዲሁም በግልፅ ማዉጣት እንዳለበት ተናግረዋል። በሌላ በኩል ጀርመንን ወክለዉ በጉባዔዉ የተሳተፉት የሙኒክና የፍራይዚንግ ጳጳስ ካርዲናል ራይንሃልድ ማርክስ ቫቲካን የወሲብ ትንኮሳ የፈፀሙ ግለሰቦችን ደብቃ ይዛለች ሲሉ ወቅሰዋል። ከ190 በላይ ጳጳሳት በተሳተፉበት በቫቲካኑ ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስትያንን ወክለዉ የጅማና ቦንጋ አገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ገብረመድሕን የተገኙ ሲሆን፤ የኤርትራ ካቶሊካዊ ቤተ-ክርስትያንን ወክለዉ ደግም የባሬንቱ አገረ ስብከት ጳጳስ ቶማስ ኦስማን ተገኝተዋል።
ተኽለ እዝጊ ገብረየሱስ
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ