ዓለማቀፉ የመጸዳጃ ቤት ቀን እና ኢትዮጵያ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 10 2006እንዲያም ሆኖ ኢትዮጵያ እስከ መጭዉ የጎርጎረሳዊ 2018 ዓ,ም ድረስ ዜጎች መጸዳጃ ቤት እንዲኖራቸዉ ጥረት ለማደግ መዘጋጀቷ ተነግሯል።
ዛሬ በተለያዩ የዓለም ሃገራት ታስቦ የዋለዉ የዓለም የመፀዳጃ ቤት ቀን በኢትዮጵያ በኦሮምያ ክልል አዳማ ከተማ በሚገኘዉ አበበ ቢቂላ ስቴድዮምም በተለያዩ ዝግጅቶች ታስቧል። በዚህ ዝግጅት ላይ ሳሉ በስልክ ያገኘናቸዉ በኢትዮጵያ በተመ የሕፃናት መርጃ ድርጅት UNICEF የዉሃ እና የግል ንፅሕና መርሃግብር ባለሞያ አቶ ሙጬ ኪዳኑ፤ እንደሚሉት ቀኑን በደማቅ ታስቦ መዋሉ እንዳለ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓትም ወደ 38 ሚሊዮን ህዝብ የመፀዳጃ ቤት ተጠቃሚ አይደለም
በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የተመ የሕፃናት መርጃ ድርጅት UNICEF የግል ንፅህናን የሚመለከተዉ መርሃግብር ተጠሪ ሳሙኤል ጎድፍሪ እንደሚሉት ዛሬ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተከበረዉ የመጸዳጃ ቤት ቀን፤ በተለይ ኢትዮጵያ ዉስጥ በንፅሕና አጠባበቅ ረገድ ትልቅ መሻሻል መታየቱን የምንገልፅበት ቀን ነዉ፤
«በተለይ ኢትዮጵያ በአፍሪቃ ከሚገኙ ሃገራት የጽዳት፤ እና የግል ንፅህናን በተመለከተ መሻሻል የታየባት ሀገር ናት፤ በመቀጠል መንግሥት እስከ መጭዉ የጎርጎረሳዉያን 2018 ዓ,ም እያንዳንዱ ነዋሪ የግል ንጽህናን ለመጠበቅ የሚያስችል እቅድ ነድፏል፤ ዩኒሴፍ በዚህ ሳምንት የሚከበረዉን የግል ንፅህና አጠባበቅ በተመለከተ በዘርፉ የሚሰሩትን የተለያዩ ተቋማትን በአንድ አሰባስቦአል።»
በዩኒሴፍ የግል ንፅህና መርሃግብር ዋና ተጠሪ፤ ሳሙኤል ጎድፍሪ፤ በንፅህና አጠባበቅ ረገድ በሚሰጠዉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ከባዱ ልማድን ማስለወጡ ነዉ፤
« ንፅህናን ለመጠበቅ በሚከናወነዉ እንቅስቃሴ ፤ ከባዱ ፈተና ይህ በሚመለከት የማህበረሰቡን ልማድ ማስለወጡ ሥራ ነዉ። ስለዚህ ይህን ለማሳካት አዲስ አካሄድ ተግባራዊ ለማድረግ በኢትዮጵያ ዉስጥ እየተሞከረ ነዉ፤ ይህም ኅብረተሰቡ ስለ ግል ንፅህና እና ጤና አጠባበቅ ዘዴ ይነጋገር የሚል ሲሆን፤ ይህም የታቀደዉን ግብ ለመምታት እንደሚረዳ ይታሰባል።» በ UNICEF የንጹህ ዉሃ እና የግል ንፅህና መርሃግብር ባለሞያ አቶ ሙጬ ኪዳኑ፤ እንደሚሉት ደግሞ ኢትዮጵያ እስከ 2018 ዓ,ም የግል ንፅህና አጠባበቅን ለማማላት የያዘችዉ መረሃ-ግብር ለእያንዳንዱ የመፀዳጃ ቤት የሚቆም ሳይሆን የንፅህና አጠባበቅን እና የመፀዳጃ ቤት ጥቅምን ለመላዉ ነዋሪ የግንዛቤ መስጠት ነዉ።
አዜብ ታደሰ
ሸዋዪ ለገሰ