1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውጥረት በአማራ እና ትግራይ ክልሎች

እሑድ፣ የካቲት 17 2011

ከቅርብ ወራት ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ የለውጥ ጅማሮች መታየታየቸው ተስፋን ቢፈጥርም በትግራይ እና አማራ ክልሎች መካከል የሚታየው ውጥረት ግን ያን ተስፋ የሚያደበዝዝ መስሏል።

https://p.dw.com/p/3DtsA
Karte Äthiopien englisch

«ፖለቲከኞች እና ተሟጋቾች ኃላፊነት ሊሰማቸው ይገባል»

የውጥረቱ መንስኤ በአንዳንዶች የአጎራባች ድንበር ግዛቶች የማንነት ጥያቄ ያስከተለው ነው የሚሉ እንዳሉ ሁሉ ይህ ውጤት እንጂ መንስኤ በማዕከላዊ መንግሥት ውስጥ የበላይነትን የማግኘት ጉዳይ እንደሆነ ይናገራሉ። የሚታየውን ችግር የየክልሉ ፖለቲከኞች እና ለክልሉ ሕዝብ ቆመናል የሚሉ አንዳንዶች ጥንቃቄ በጎደለው መልኩ የሚሰነዝሩት አስተያየት እያባባሰው መሆኑንም ያመለክታሉ። ይህ አካሄድም ወዴት ያመራ ይሆን የሚል ስጋትን አስከትሏል። DW ተጎራባች በሆኑት የአማራ እና ትግራይ ክልሎች መካከል የሚታየውን ውጥረት እና ስጋት፤ ያንን ለማርገብም ሊደረጉ ስለሚገባቸው የመፍትሄ ሃሳቦች ለማንሳት የሞከረ ውይይት አካሂዷል። ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባው ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ