ውጤት ያላስገኘው የደቡብ ሱዳን ውይይት
ሐሙስ፣ ግንቦት 16 2010ማስታወቂያ
የአደራዳሪነቱን ሚና የያዘው የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት እንደገለጸው፣ ተቀናቃኞቹ ወገኖች በስልጣን መጋራቱ እና በፀጥታ ጥበቃ ጉዳዮች ላይ አስማሚ ሀሳብ ላይ በመድረስ የርስ በርሱን ጦርነት እንዲያበቁ ቀናት በተጠናከረ ሁኔታ ያደረገው ጥረት ፍሬ ሳያስገኝ ቀርቷል። በድርድሩ የተገኙት የኖርዌይ፣ የዩኤስ አሜሪካ እና የብሪታንያ ተወካዮች ኢጋድ ተቀናቃኖቹን ወገኖች ለማግባባት የጀመረውን ጥረት እንዲገፋበት ጠይቀዋል። በርስበርሱ ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን የተገደሉ ሲሆን፣ ሚልዮኖችም ተፈናቅለዋል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ