1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዉይይት፤ የኢትዮጵያ ጦርነትና የዲፕሎማሲዉ ጫና

እሑድ፣ ጥቅምት 14 2014

የዉይይቱ ተሳታፊዎች፣ አቶ ፍፁም አረጋ፣ በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር፤አቶ ጥሩነሕ ገምታ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የፅሕፈት ቤት ኃላፊ፤አቶ ባይሳ ዋቅወያ፣ የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሙያና የቀድሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣን ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/424ss
Äthiopien Soldaten der äthiopischen Nationalen Verteidigungskräfte (ENDF)
ምስል AMANUEL SILESHI/AFP/Getty Images

«ድርድር ሽንፈት ዓይደለም፣ድርድር ስልጣኔ ነዉ----» አቶ ባይሳ ዋቅ ወያ

ትግራይ ዉስጥ የዛሬ ዓመት ጥቅምት የተጀመረዉ ጦርነት አድማሱን አስፍቶ የአማራና የአፋር ክልልሎችን አዳርሷል።የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ወገኖች እንደሚገምቱት ጦርነቱ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት፣ በቢሊዮን ብር የሚገመት ሐብትና ንብረት አጥፍቷል።10 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ አፈናቅሏል፤ አሰድዷል፣ ለረሐብ አጋልጧልም።

 

ዉጊያ በሚደረግባቸዉና ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በሚቆጣጠራቸዉ አካባቢዎች የመብራት፣የስልክ፣ የትራንስፖርት፣ የሕክምና አገልግሎት የለም።ትምሕርት፣እርሻና ንግድም ባብዛኛዉ ተቋርጧል ወይም ቀንሷል።ከትግራይና ከዋግ ሕምራ ዞን ሰሞኑን የተሰራጩ ዘገቦች እንደሚያመለክቱት ሕፃናትና አቅመ ደካሞች በረሐብና በመድሐኒት እጦት እየሞቱ ነዉ።ጦርነቱ ወትሮም የተዳከመዉን የሐገሪቱን ምጣኔ ሐብት እያሽመደመደዉ ነዉ።

Internally displaced Persons in Dessie
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በዓለም በተለይም በአፍሪቃዉያን ዘንድ የነፃነት አብነት፣ የረጅም ጊዜ የመንግሥትነት ምሳሌ፣የዲፕሎማሲ ማዕከል የነበረችዉን ሐገር በምዕራባዉያን የተገለለች፣ከተባበሩት መንግስታት  ድርጅት ጋር ሳይቀር የዲፕሎማሲ እሰጥ አገባ የገጠመች፣ የብዙ ሚሊዮን ተመፅዋቾች መኖሪያ አድርጓታል።

 

ማዕቀብም ተጥሎባታል።ተፋላሚ ኃይላት ዉጊያ አቁመዉ ካልተደራደሩ ዩናያይትድ ስቴትስና የአዉሮጳ ሕብረት በኢትዮጵያ በመንግስትና በሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) ባለሥልጣናት ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ለመጣል እየዛቱ፣ ሌሎች መንግስታትንም እያስተባበሩ ነዉ።ተፋላሚዎች ግን እስካሁን ጦርነቱን ለማቆም የፈቀዱ አይመስሉም።ለምን? እና ደግሞስ እስከመቼ? የጦርነቱ ሒደትና የዲፕሎማሲዉ ግፊት የዛሬ ዉይይታችን ትኩረት ነዉ።ሶስት እንግዶች አሉን።

Äthiopien | Erneuter Luftangriff auf Hauptstadt von Tigray
ምስል AP Photo/picture alliance
  1. አቶ ፍፁም አረጋ፣ በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር
  2. አቶ ጥሩነሕ ገምታ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የፅሕፈት ቤት ኃላፊ
  3. አቶ ባይሳ ዋቅወያ፣ የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሙያና የቀድሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣን ናቸዉ።

 

ነጋሽ መሐመድ