ዉኃን ለጤና መጠጣት
ማክሰኞ፣ ግንቦት 4 2007ማስታወቂያ
«ጤና ከገንዘብ ዉኃን ከቀለብ የሚቆጥረዉ የለም» ይላሉ አበዉ። ለዚህም ይመስላል ብዙዎች ለምግብ እና ለሌሎች መጠጦች የሚሰጡትን ስፍራ ያህል ለዉኃ ሲሰጡ የማይታየዉ። ዉኃ ስለመጠጣት ልምዳችሁ አጋሩን ስንል በፌስ በኩክ ገጻችን ላይ ላቀረብንላችሁ ጥያቄ የሰጣችሁት ምላሽም እንደተመለከታችሁት ይህንን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። በየዕለቱ አስበዉ በቂ ዉኃን የመጠጣት ልምድ ያላቸዉ ብዙዎች አይደሉም። ሲቀልዱ ይሁን ወይም ከምር ለማወቅ ቢከብደንም በሳምንት አንዴ ያሉ፤ ዉኃ በፈረቃ በሆነባት ከተማ ዉኃን እንደልብ መጠጣት የማይታለም እንደሆነ የጠቆሙ፤ ንፁሕ የመጠጥ ዉኃን ማግኘት ቅንጦት የሆነበት አካባቢ መኖሩን ያስረዱም አልጠፉም። የዉኃ እንደልብ አለመገኘት ግን ዉኃ ለሰዉነታችን ጤና ወሳኝ መሆኑን አያጎድለዉም። ግን የተከበሩ አድማጮቻችን ያነሷቸዉ የመሠረተ ልማትና ማኅበራዊ ጉዳዮች ከሚመለከተዉ አካል ትኩረትን የሚሹ መሆናቸዉ አያነጋግርም። ይህን ርዕሰ ጉዳይ ያነሳንበት ዓላማ ዉኃ በጤንነታችን ላይ ስለሚኖረዉ ሚና ለማሳሰብ በመሆኑ እሱዉ ላይ እናተኩር። ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ