1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወጣቱ ከኦባማ ጉብኝት የሚጠብቀው

ዓርብ፣ ሐምሌ 17 2007

በስልጣን ላይ ያለ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን ሲጎበኝ ባራክ ኦባማ የመጀመሪያው መሪ ናቸው። ለመሆኑ ወጣቱ ስለ ኦባማ ጉብኝት ምን ያስባል? ጥቂት ወጣቶች ያላቸውን አስተያየት አካፍለውናል።

https://p.dw.com/p/1G4Nv
Kenia Besuch Obama Nairobi wird herausgeputzt
ምስል picture-alliance/dpa/D. Irungu

ወጣቱ ከኦባማ ጉብኝት የሚጠብቀው

ከኬንያዊ አባት የተወለዱት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ኦባማ እሁድ ዕለት ወደ ኢትዮጵያ በመጓዝ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ እና ከፕሬዚዳንት አቶ ሙላቱ ተሾመ ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል። አርብ ዕለት ወደ ኬንያ የተጓዙት ኦባማ፤ በስልጣን ዘመናቸው ለአፍሪቃ ከፍተኛ ድጋፍ ያበረክታሉ ተብሎ ተጠብቋል።

አንድ በስልጣን ላይ ያለ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን ሲጎበኝ ባራክ ኦባማ የመጀመሪያው መሪ እንደመሆናቸው ወጣት ኢትዮጵያውያን ስለ ጉብኝቱ ያላቸውን አስተያየት ምንድን ነው?

የፕሬዚዳንት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ በተለይም ወደ አዲስ አበባ መምጣት የሚደግፍ እና የሚቃወም አስተያየቶችን አግኝተናል።

እነዚህኑ አስተያየቶች ከዝግጅቱ የድምፅ ዘገባ ያገኛሉ።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ