ወታደራዊ ሹም ሽር በሳዑዲ
ረቡዕ፣ የካቲት 21 2010ማስታወቂያ
በተለይ በከፍተኛ የጦር አመራሮቹ ሹም ሽር በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው፡፡ መውጫ ያጣውን የየመን ጦርነት በተለየ ዘይቤ ለማስተናገድ ነው የሚሉ መላ ምቶች ባንድ በኩል ፤ ለወጣቱ አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሰልማን ቀጣይ ስልጣን መንገድ መጥረግ የሚሉት በሌላ በኩል አስተያየቶቹን ይመራሉ፡፡
በሚቀጥለው ሳምንት በእንግሊዝ ጉብኝት ለማድረግ መርሐ ግብር የያዙት አልጋወራሽ መሀመድ ቢን ሰልማን በየመን በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሳዑዲ መራሹ ወታደራዊ ኃይል በሚያደርሰው ተደጋጋሚ ጥቃት ተደጋጋሚ ነቀፌታ ለሚያደርሱባቸው የአሜሪካ እና የአውሮጳ ባለስልጣናት ለውጥ ማድረጋቸውን ለመግለጽ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ተንታኞች ያብራራሉ፡፡ ከሪያድ ስለሺ ሽብሩ ተጨማሪ ዘገባ አለው
ስለሺ ሽብሩ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ