ወቅቱን ያልጠበቀዉ ዝናብ በሐረሪ
ሐሙስ፣ ኅዳር 5 2006ማስታወቂያ
ከዚህም ሌላ በዚሁ ዝናብ ምክንያት ከሃያ የሚበልጡ ቤቶች ፈራርሰዋል። የክልሉ የምግብ ዋስትናና አደጋ መከላከል ቢሮ በበኩሉ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሚኖር ማስጠንቀቂያዉን አሰራጭቻለሁ፤ ይህንን ተጠቅሞም አርሶ አደሩ ምርቱን እየሰበሰበ ነዉ ይላል። መስሪያ ቤቱም አስፈላጊዉን ድጋፍም እያደረገ መሆኑን ይገልጻል። በሌላ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ አርሶ አደሮች ደግሞ ሰብሉ ከመጎዳቱ አስቀድመዉ በዘመቻ ለመሰብሰብ እየሞከሩ እንደሚገኙ ተነግሯል። ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ